የፕሮግራሙ ይዘት
አካል ጉዳተኛ ሴት ተመራቂ ተማሪዋችን የእውቅና ግዜ መስጠት
የ2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ብራንች ተመራቂ ተማሪዋች በዛሪው እለት በቡና ጠጡ ፕሮግራም የእውቅና ፕሮግራም እንዲሁም ያለፉበትን መንገድ በጥቂት ልምዳቸውን ያካፈሉበት እለት ነበር። ተማሪዋቹ በትምህርት ወቅት የነበራቸውን ፈተና በተለይ ከአካል ጉዳት ጋር በተያያዘ ፈተና ቢገጥማቸውም ፈተናቸውን ተቋቁመው ለዚህ የማዕረግ ውጤት በመድረሳቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልፀዋል።
በፕሮግራሙም የኢውድና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ድባቤ ባጫ የማበረታቻ እና ለማህበሩ ተሳታፊዋች በርትተው እንዲማሩ እነዚህን ወጣቶች በማየት በርትተው እንዲማሩ እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ለልጆቻቸው ስኬት ትልቁን ሚና በመጫወታቸው ይህ ስኬት የወላጆቻቸውም እንደሆነ አክለው አመስግነዋል።
ተማሪ ያብስራ ሽፈራው የእንቅስቃሴ አካል ጉዳት ያለባት ተመራቂ ስትሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሳይኮሎጂ በከፍተኛ ማዕረግ 3̋.5 አምጥታለች። ተማሪ ያብስራ በንግግሯ
“ለኔ ፈተና ልክ እንደ ሜካፕ ነው፤ ሰው በሜካፕ እንደሚያምር ሁሉ እኔም በሚገጥሙኝ ፈተናዋች የበለጠ እዋባለው” ብላለች እንዲሁም “አካል ጉዳተኘነት አለመቻል አይደለም እንችላለን እንችላለን እንችላለን !!!!!!” በማለት ደስታዋን ገልፃለች
ተማሪ ትግሰት ሰለሞን የእንቅስቃሴ አካል ጉዳት ያለባት ተመራቂ ስትሆን በGBC collage በቲዋሎጂ 3̌.76 በማምጣት የማዕረግ ተመራቂ ሆናለች። ትግስትም የነበረባትን ፈተና በትግስት ተወታ እዚ መድረሷን አክላ አካል ጉዳት አለመቻል እንዳልሆነ አስረግጣ ተናግራለች።
ተማሪ መቅደስ ነብሮ በከፊል መስማት የተሳናት ተመራቂ ስትሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በብሮድ ካስት ጆርናሊዝም 3̋.2 አምጥታለች።
ተማሪ አበራሽ ገረመው የእንቅስቃሴ አካል ጉዳት ያለባት ተመራቂ ስትሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማኔጅመንት 3̋.1 አምጥታለች።
ተማሪ ፋንታዬ መኮንን አይነስውር ተመራቂ ስትሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማኔጅመንት 3̋.1 አምጥታለች።
ኢውድና ለተመራቂ ተማሪዋች የተሰማትን ታላቅ ደስታ በመግለፅ “አካል ጉዳተኝነት አለመቻል” አለመሆኑን ስላሳያችሁን እጅግ በጣም ኮርተንባችሀል።
ቡና ጠጡ
26/10/2017
Hi, this is a comment.
To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
Commenter avatars come from Gravatar.